Ethio China primary and Middle School

Your valuable insights are crucial in helping us gain a deeper understanding.

Take a survey

  እንኳን ወደ ኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በደህና መጡ!

  • ትምህርት ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ፣ ለመልካም አስተዳደር ማስፈን እና ለዘላቂ ልማት መፋጠን ቁልፍ መሳሪያ መሆኑ ይታወቃል፡፡
  • ትምህርት ይህንን ሚና በተገቢው ሊጫወት የሚችለው ጥራቱ ተጠብቆ ሲሰጥ እና ብቁ ዜጋ ማፍራት ሲቻል ብቻ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በሃገራችን የትምህርተ አቅርቦት ለሁሉም ዜጎች በፍትሃዊነት ለማዳረስ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተነድፎ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲውም ድህነትን ለማጥፋትና ሃገሪቱን በልማት ጎዳና ከተራመዱ ሃገሮች ተርታ ለማሰለፍ እንደ ሀገር የተቀመጠውን እራዕይ መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ ከዚህ አጠቃላይ ማዕቀፍ አንፃር በከተማችን የተከናወኑ መጠነ ሰፊ ስራዎች ባለፉት ዓመታት የከተማችንን የትምህርት ተሳትፎና ፍትሃዊነት በማሳደግ ረገድ አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን የሚሰጠው ትምህርት ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን በማድረግ በሁሉም በጅምር ደረጃ የተሻሉ ውጤቶችን ማየት ተችሏል፡፡
  • ከትምህርት ቤታችን የትምህርት ስራ በተደራሽነቱ እና በፍትሃዊነቱ ረገድ መሰረታዊ ለውጦች የታዩበት ቢሆንም በጥራቱ ረገድ ሰፊ ስራዎች መሰራት እንዳለበት ይታመናል፡፡ ከዚህ መነሻ የአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ በተቀረፀው ልክ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ ፓኬጁን መተግበር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ትምህርት ቤታችን የመምህር ብቃትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስልጠናዎች መሰጠታቸው ፣ ለመምህራን ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት መስጠት የሚያስችላቸው የቅድመ ስራና የስራ ላይ ስልጠና መሰጠቱ ፣ ስርዓተ ትምህርቱ ከትምህርት ደረጃ የሚጠበቀውን ፕሮፋይል ሊያስጨብጥ የሚችል መሆኑም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸው ፣ አቻ ለአቻ ውይይቶችን በማድረግ የትምህርት አደረጃጀትና አሰራር እንዲፈጠር በማድረግ ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣትና ተሞክሮን ለመለዋወጥ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸው እንደዚሁም ይህን ለማጠናከር በክትትልና ድጋፍ ተግባራት እንዲታጀቡ ለማድረግ ጥረት መደረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ ከሚጠበቀው አጠቃላይ ውጤት አንፃር ሲታይ የተመዘገበው ውጤት በቂ ነው ማለት አይቻልም፡፡
  • ስለዚህ ሃገራዊ ህዳሴ እውን የሚያደርግ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑን የሚያሳዩ ተስፋ ሰጪ ለውጦች መታየት በመጀመራቸው ይህንን ደግሞ የማስቀጠል ሃላፊነት የሁሉም የትምህርት ባለድርሻ ማለትም በየደረጃው ያለው የትምህርት አመራር ፣ መምህራን ፣ ተማሪዎች ፣ ወላጆች የግል ባለሃብቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሃላፊነት ስለሆነ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ በጋራ እንረባረብ እላለሁ፡፡
  • መ/ር ክብሩ እንግዳ 
  • የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት ትምህርት ቤት ዋና ር/መምህር

Gallery

Notice

03 Jun 2025
Mark Record

ማሳሰቢያ

አሁን

ከአይሲት ክፍል በደረሰን መረጃ ብዙ መ/ራን በተለይም ከ5ኛ ክፍል በላይ የሚያስተምሩ የተማሪዎችን ውጤት ወደ ሲስተም የማስገባትስራ እየጨረሳችሁ እንደሆነ መገንዘብ ችለናል፡፡ በዚህ..

07 Apr 2025
BSC ውጤት

ለሁሉም  ት/ት ክፍል ተጠሪ

 የመጋቢት ወር  የመምህራን BSC ውጤት ሰርታችሁ እስከ 2/8/2017ዓ.ም  ድረስ ገቢ እንድታደርጉ እያሳሰበን በተቀመጠው ቀን ውጪ የምመጣው ውጤት ተቀባይነት አይኖርም ተጠያቂ..

04 Apr 2025
E-school Training

ከዝ በፊት እ-ስኩል ስልጠና ያልወሰደችው መ/ራን  26/07/2017 ዓ.ም ጠዋት 5:30 ስልጠና ስላለ ICT ክፍል እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን። 

  Barsiisonni kana dura leenjii..

FAQ support

We're here to power your growth!

We make sure you have everything you need to succeed as a trainer and edupreneur.

Raise your question
Wiki
Knowledge management
Book
Digitial library

Copyright © All rights reserved.

Created with